Amos 8

የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት

1ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ እነሆ፤ የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት ነበረ። 2እርሱም፣ “አሞጽ ሆይ፤ ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም፣ “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልሁ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቷል፤ ከእንግዲህም አልምራቸውም።”

3ጌታ እግዚአብሔር፣ “በዚያ ቀን የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ወደ ዋይታ
የቤተ መቅደሱ ዘማርያን ዋይታ ያሰማሉ የሚሉ አሉ።
ይለወጣል፤ እጅግ ብዙ የሆነ የሰው ሬሳ ወድቆ ይገኛል፤ ዝምታም ይሰፍናል” ይላል።

4እናንት ችግረኞችን የምትረግጡ፣
የምድሪቱንም ድኾች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤
5እንዲህም ትላላችሁ፤

“መስፈሪያውን በማሳነስ፣
ዋጋውን ከፍ በማድረግ፣
በሐሰተኛ ሚዛን በማጭበርበር፣
እህል እንድንሸጥ፣
የወር መባቻ መቼ ያበቃል?
ስንዴም ለገበያ እንድናቀርብ፣
ሰንበት መቼ ያልፋል?”
6ድኻውን በብር፣
ችግረኛውንም በጥንድ ጫማ እንገዛለን፤
ግርዱን እንኳ በስንዴ ዋጋ እንሸጣለን።
7 እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እንዲህ ሲል ምሏል፤ “እነርሱ ያደረጉትን ሁሉ ከቶ አልረሳም።

8“በዚህ ነገር ምድር አትናወጥምን?
በውስጧ የሚኖሩትስ ሁሉ አያለቅሱምን?
የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤
እንደ ግብፅ ወንዝም ወደ ላይ ይፈናጠራል፤
ተመልሶም ይወርዳል።”
9ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“በዚያ ቀን፣ ፀሓይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤
ምድርንም ደማቅ ብርሃን ሳለ በቀን አጨልማታለሁ።
10ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣
ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤
ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣
ጠጕራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤
ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣
ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።”

11ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፤
ይኸውም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ራብ እንጂ፣
እንጀራን የመራብ ወይም ውሃን የመጠማት አይደለም።
12ሰዎች እግዚአብሔርን ለመሻት፣
ከባሕር ወደ ባሕር፣
ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይንከራተታሉ፤
ነገር ግን አያገኙትም።
13“በዚያ ቀን፣

“ቈነጃጅት ሴቶችና ብርቱዎች ጕልማሶች፣
ከውሃ ጥም የተነሣ ይዝላሉ።
14በሰማርያ ኀፍረት
ወይም በአሼማ ወይም በጣኦት አማልክት
የሚምሉ፣
ወይም፣ ‘ዳን ሆይ፤ ሕያው አምላክህን’ የሚሉ፣
ወይም ‘ሕያው የቤርሳቤህ አምላክን
ወይም መንገዱን
’ ብለው የሚምሉ፣
ዳግመኛ ላይነሡ፣ ለዘላለም ይወድቃሉ።”
Copyright information for AmhNASV