Psalms 100

እግዚአብሔርን ለማመስገን የቀረበ ግብዣ

የምስጋና መዝሙር።

1ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤
2 እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤
በፍሥሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ።
3 እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤
እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፤
እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን።

4በምስጋና ወደ ደጆቹ፣
በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤
አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤
5 እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤
ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
Copyright information for AmhNASV