Psalms 43

በስደት ላይ ያለ ሌዋዊ ልቅሶ

1አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤
ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፤
ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።
2አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣
ለምን ተውኸኝ?
ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣
ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?
3ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤
እነርሱ ይምሩኝ፤
ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣
ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ።
4እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤
ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣
በበገና አመሰግንሃለሁ።
5ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?
ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?
ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤
አዳኜና አምላኬን፣
ገና አመሰግነዋለሁና።
Copyright information for AmhNASV