Psalms 89

መዝሙርና ለእግዚአብሔር ታማኝነት የቀረበ ጸሎት

የይዝራኤላዊው የኤታን ትምህርት።

1ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ለዘለላለም እዘምራለሁ፤
በአፌም ታማኝነትህን ከትውልድ እስከ ትውልድ እገልጻለሁ።
2ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣
ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁ።
3አንተም እንዲህ ብለሃል፤ “ከመረጥሁት ጋር ኪዳን ገብቻለሁ፤
ለባሪያዬ ለዳዊት ምያለሁ፤
4‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤
ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ

5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣
ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤
6በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋር ማን ሊስተካከል ይችላል?
ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?
7እግዚአብሔር በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በጣም የሚፈራ፣
በዙሪያውም ካሉት ሁሉ በላይ እጅግ የሚከበር ነው።
8የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ታማኝነትህም ከብቦሃል።

9የባሕርን ቍጣ ትቈጣጠራለህ፤
ሞገዱም ሲነሣ ጸጥ ታደርገዋለህ።
10አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤
በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።
11ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤
ዓለምንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አንተ መሠረትህ።
12ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ሐሤት ያደርጋሉ።
13አንተ ክንደ ብርቱ ነህ፤
እጅህ ኀያል ናት፤ ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለች ናት።

14ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤
ምሕረትና ታማኝነት በፊትህ ይሄዳሉ።
15 እግዚአብሔር ሆይ፤ እልልታን የሚያውቅ፣
በፊትህም ብርሃን የሚሄድ ሕዝብ ምስጉን ነው።
16ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል፤
በጽድቅህም ሐሤት ያደርጋሉ፤
17አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤
በሞገስህም ቀንዳችንን
የጥንካሬ ምልክት ነው።
ከፍ ከፍ አደረግህ።
18ጋሻችን
ወይም ልዑል ማለት ነው።
የእግዚአብሔር ነውና፤
ንጉሣችንም የራሱ የእስራኤል ቅዱስ ነው።

19በዚያን ጊዜ በራእይ ተናገርህ፤
ታማኝ ሕዝብህንም እንዲህ አልህ፤
“ኀያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁት፤
ከሕዝብ መካከል የተመረጠውንም ከፍ ከፍ አደረግሁት።
20ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፤
በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት።
21እጄ ይደግፈዋል፤
ክንዴም ያበረታዋል።
22በጠላት አይበለጥም፤
ክፉ ሰውም አይበግረውም።
23ባላንጣዎቹን በፊቱ አደቅቃቸዋለሁ፤
ጠላቶቹንም እቀጠቅጣለሁ።
24ታማኝነቴና ምሕረቴ ከእርሱ ጋር ይሆናል፤
በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።
25እጁን በባሕር ላይ፣
ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።
26እርሱም፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤
አምላኬና መዳኛ ዐለቴም ነህ’ ብሎ ይጠራኛል።
27እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፤
ከምድር ነገሥታትም በላይ ከፍ ይላል።
28ምሕረቴንም ለዘላለም ለእርሱ እጠብቃለሁ፤
ከእርሱ ጋር የገባሁት ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።
29የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣
ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ።

30“ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣
ደንቤን ባይጠብቁ፣
31ሥርዐቴን ቢጥሱ፣
ትእዛዜንም ባያከብሩ፣
32ኀጢአታቸውን በበትር፣
በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።
33ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፤
ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።
34ኪዳኔን አላፈርስም፤
ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።
35አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣
ዳዊትን አልዋሸውም።
36የዘር ሐረጉ ለዘላለም፣
ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሓይ ጸንቶ ይኖራል፤
37በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው፣
እንደ ጨረቃ እርሱ ለዘላለም ይመሠረታል።” ሴላ

38አሁን ግን ናቅኸው፤ ጣልኸውም፤
የቀባኸውንም እጅግ ተቈጣኸው።
39ከባሪያህ ጋር የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ፤
የክብር ዘውዱን ትቢያ ላይ ጥለህ አቃለልኸው።
40ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፤
ምሽጉንም ደመሰስህ።
41ዐላፊ አግዳሚው ሁሉ ዘረፈው፤
ለጎረቤቶቹ መዘባበቻ ሆነ።
42የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረግህ፤
ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው።
43የሰይፉን ስለት አጠፍህ፤
በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም።
44ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤
ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው።
45የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው፤
ዕፍረትንም አከናነብኸው። ሴላ

46 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን?
ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነድደው እስከ መቼ ነው?
47ዘመኔ ምን ያህል ዐጭር እንደ ሆነች ዐስብ፤
የሰውን ልጆች እንዲያው ለከንቱ ፈጠርሃቸው!
48ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ የሚቀር
ሰው አለን?
ራሱን ከሲኦል እጅ ማዳን የሚችል ማን ነው? ሴላ
49ጌታ ሆይ፤ ለዳዊት በታማኝነትህ የማልህለት፣
የቀድሞው ምሕረትህ የት አለ?
50ጌታ ሆይ፤ ባሪያህ
ባሮችህ የሚሉ አሉ።
እንዴት እንደ ተፌዘበት፣
የብዙ ሰዎችንም ነቀፋ እንደ ታቀፍሁ ዐስብ።
51 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ የተሣለቁበትን፣
የቀባኸውን ሰው ርምጃ የነቀፉበትን ሁኔታ ዐስብ።


52 እግዚአብሔር ለዘላለም ይባረክ፤
አሜን፤ አሜን።
Copyright information for AmhNASV