‏ 1 Kings 7

ሰሎሞን ቤተ መንግሥቱን ሠራ

1ሰሎሞን የራሱን ቤተ መንግሥት ሠርቶ ለመጨረስ ዐሥራ ሦስት ዓመት ፈጀበት። 2የሊባኖስ ዱር የተባለ ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ይህም ርዝመቱ
ርዝመቱ 46 ሜትር፣ ወርዱ 23 ሜትር እንዲሁም ቁመቱ 13.5 ሜትር ያህል ነው።
መቶ ክንድ፣ ወርዱ አምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ ሲሆን፣ በአራት ረድፍ የቆሙ የዝግባ ምሰሶዎች ደግፈው የያዟቸው አግዳሚ የዝግባ ተሸካሚዎች ነበሩት።
3ቤቱ ከምሰሶዎቹ ላይ ያረፉ አግዳሚ ተሸካሚዎች አሉት፤ በእያንዳንዱ ዐምድ ላይ ዐሥራ አምስት፣ በድምሩ አርባ አምስት ተሸጋጋሪዎች ሲኖሩ፣ ከእነዚህም ተሸጋጋሪዎች በላይ ከዝግባ የተሠራ የጣሪያ ክዳን ነበር። 4መስኮቶቹም ከፍ ብለው የተሠሩ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ ነበሩ። 5በሮቹ በሙሉ ባለ አራት ማእዘን መቃኖች ያሏቸው፣ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ
በዕብራይስጥ የክፍሉ መልእክት በትክክል አይታወቅም።
ነበሩ።

6ሰሎሞን፣ “ባለ ብዙ ምሰሶ አዳራሽ” የተባለ ቤት ሠራ፤ የዚህም ርዝመቱ አምሳ ክንድ፣ ወርዱ ሠላሳ ክንድ፣
ርዝመቱ 23 ሜትር፣ ወርዱ 13.5 ሜትር ያህል ነው።
ነበር፤ በስተ ፊት በኩልም ጣራ ያለውና በአዕማድ የተደገፈ መመላለሻ ነበረው።

7ዳኝነት የሚያይበትንም የዙፋን ችሎት አዳራሽ ሠራ፤ ይኸውም የፍትሕ አዳራሽ የተባለው ነው፤ ይህንም ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው
ቩልጌትና የሱርስቱ ትርጕም ከዚህ ጋር ሲስማሙ ዕብራይስጡ ግን፣ ወለል ይላል።
ድረስ በዝግባ ሳንቃ ሸፈነው።
8ከአዳራሹ በስተ ጀርባ ባለው አደባባይ መኖሪያው እንዲሆን የተሠራው ቤተ መንግሥትም የዚሁ ተመሳሳይ ነበር። ሰሎሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ይህንኑ ቤተ መንግሥት የመሰለ አዳራሽ ሠራ።

9ከውጭ አንሥቶ እስከ ትልቁ አደባባይ፣ ከመሠረቱ አንሥቶ እስከ ድምድማቱ ያለው የሕንጻ ሥራ በሙሉ፣ በውስጥም በውጭም በልክ በልኩ በተቈረጠና አምሮ በተስተካከለ ምርጥ ድንጋይ የተሠራ ነበር። 10መሠረቱም ዐሥርና
4.5 ሜትር ያህል ነው።
ስምንት ክንድ
3.6 ሜትር ያህል ነው።
ርዝመት ባላቸውና ምርጥ በሆኑ ታላላቅ ድንጋዮች የተሠራ ነበር።
11በላዩም ላይ ምርጥ የሆኑ፣ በልክ በልኩ የተቈረጡ ድንጋዮችና የዝግባ ሳንቃዎች ነበሩ። 12የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጠኛ አደባባይ ከመመላለሻ በረንዳው ጭምር እንደ ትልቁ አደባባይ አምሮ በተጠረበ ሦስት ረድፍ ድንጋይና ተስተካክሎ በተከረከመ በአንድ ረድፍ የዝግባ ሳንቃ የታጠረ ነበር።

የቤተ መቅደሱ ዕቃዎች

7፥23-26 ተጓ ምብ – 2ዜና 4፥2-5 7፥38፡40-51 ተጓ ምብ – 2ዜና 4፥6፡10–5፥1 13ንጉሥ ሰሎሞንም መልእክተኛ ልኮ ኪራም
በዚህ ስፍራ እንዲሁም በ40 እና 45 ላይ ኪራም የሚለው ዕብራይስጡ ሂራም ይለዋል።
የተባለውን ሰው ከጢሮስ አስመጣ፤
14የኪራም እናት ከንፍታሌም ነገድ ስትሆን፣ እርሷም መበለት ነበረች፤ አባቱ የጢሮስ ሰው ሲሆን፣ የናስ ሥራ ባለሙያ ነበር። ኪራም በማናቸውም የናስ ሥራ ጥበብን፣ ማስተዋልንና ዕውቀትን የተሞላ ሰው ነበር፤ እርሱም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን መጥቶ የተመደበለትን ሥራ ሁሉ አከናወነ።

15ኪራም የእያንዳንዱ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ ዙሪያው ዐሥራ ሁለት ክንድ
ቁመቱ 8.1 ሜትር፣ ዙሪያው 5.4 ሜትር ያህል ነው።
የሆነ፣ ሁለት የናስ ምሰሶዎች ሠራ።
16እንዲሁም በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ የሚሆኑ፣ ሁለት ጕልላት ከቀለጠ ናስ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ
በዚህና በ23 ላይ 2.3 ሜትር ያህል ነው።
ነበር።
17በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ ላሉት ጕልላቶችም ጌጥ እንዲሆኑ፣ ለእያንዳንዳቸው ሰባት የመረብ ሰንሰለት አበጀ፤ 18ደግሞም በምሰሶዎቹ ላይ ያሉትን ጕልላቶች ለማስጌጥ የእያንዳንዱን መረብ ዙሪያ የሚከብቡ ሮማኖች በሁለት ረድፍ
ሁለት የዕብራይስጥ ቅጆችና የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋር ሲስማሙ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ በሁለት ረድፍ አዕማዶች ሥራ ይላሉ።
ሠራ፤ ለሁለቱም ጕልላቶች
ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆችና የሱርስቱ ትርጕም ከዚህ ጋር ሲስማሙ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ሮማኖች ይላሉ።
ያደረገው ተመሳሳይ ነበር።
19በመመላለሻው ምሰሶዎች ዐናት ላይ ያሉት ጕልላቶች ቁመታቸው አራት ክንድ
በዚህና በ38 ላይ 1.8 ሜትር ይላል።
ሲሆን፣ የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበራቸው።
20በሁለቱም የምሰሶ ጕልላቶችና ከመርበቡ ቀጥሎ ባለው የክብ ቅርጽ ላይ ዙሪያውን በሙሉ ሁለት መቶ ሮማኖች በተርታ ነበሩ። 21ምሰሶዎቹንም በቤተ መቅደሱ መመላለሻ ላይ አቆመ፤ በስተ ደቡብ ያቆመውን ምሰሶ ያኪን፣
ምናልባት አነጸ ማለት ሊሆን ይችላል።
በስተ ሰሜን በኩል ያለውንም ቦዔዝ
ምናልባት በእርሱ ዘንድ ጥንካሬ አለ ማለት ሊሆን ይችላል
ብሎ ጠራው።
22ዐናቱ ላይ ያሉት ጕልላቶች የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበራቸው። የምሰሶዎቹም ሥራ በዚህ ሁኔታ ተፈጸመ።

23ቅርጹ ክብ፣ ስፋቱ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፣
4.5 ሜትር ያህል ነው።
ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ ክብ ገንዳ ከቀለጠ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ
13.5 ሜትር ያህል ነው።
ሆነ።
24ከከንፈሩም ዝቅ ብሎ፣ በእያንዳንዱ ክንድ ላይ እንደ ቅል ያሉ ዐሥር ቅርጾች ዙሪያውን በሁለት ረድፍ ከብበውታል፤ እነዚህም ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ተሠርተው ነበር።

25ገንዳውም፣ ሦስቱ ፊታቸውን ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ባዞሩ የዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስሎች ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ገንዳው በላያቸው ሆኖ የሁሉም የኋላ አካል በመካከል ላይ የገጠመ ነበር። 26የገንዳው ውፍረት አንድ ጋት
8 ሴንቲ ሜትር ያህል ነው።
ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ እንደ አበባ ቅርጽ ሆኖ፣ የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም አርባ ሁለት ሺሕ ሊትር
44 ኪሎ ሊትር ያህል ነው። የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ይህን ዐረፍተ ነገር አይጨምርም።
ያህል ውሃ የሚይዝ ነበር።

27እንዲሁም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ዐሥር ባለ መንኰራኵር የዕቃ ማስቀመጫዎች ከመዳብ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ርዝመት አራት ክንድ፣ ወርድ አራት ክንድ፣ ቁመትም ሦስት ክንድ
ርዝመቱና ወርዱ 1.8 ሜትር ያህል ሲሆን ቁመቱ 1.3 ሜትር ያህል ነው።
ነበር።
28የዕቃ ማስቀመጫዎቹ የተሠሩት እንደዚህ ነው፤ እነዚህም ቀጥ ብለው ከቆሙ ደጋፊዎች ጋር የተያያዙ ባለ አራት ማእዘን ጠፍጣፋ ናሶች ነበሯቸው። 29ዳርና ዳር ባሉት ድጋፎች መካከል በሚገኙት ጠፍጣፋ ናሶች ላይ የአንበሶችን፣ የኮርማዎችንና የኪሩቤልን ምስል አደረገ፤ በድጋፎቹም ላይ እንደዚሁ አደረገ። ከአንበሶቹና ከኮርማዎቹ በላይና በታች በኩል ደግሞ የአበባ ጕንጕን የሚመስሉ ተቀጥቅጠው የተሠሩ ቅርጾች ነበሩ። 30እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት የናስ መንኰራኵርና መንኰራኵሮቹ የሚሽከረከሩባቸው የናስ ወስከምቶች እንዲሁም እያንዳንዳቸው በአራቱም ማእዘን ገጽ ላይ የአበባ ጕንጕን ቀልጦ የተሠራባቸው የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበረው። 31በዕቃ ማስቀመጫዎቹም ውስጥ ጥልቀቱ አንድ ክንድ
0.5 ሜትር ያህል ነው።
የሆነ ባለ ክብ ክፍተት ነበር፤ ይህም ክፍተት ድቡልቡል ሆኖ ከታች ከመቆሚያው በኩል ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል
በዚህና በ32 ላይ 0.7 ሜትር ያህል ነው።
ወርድ ሲኖረው፣ በክፍተቱም ዙሪያ ቅርጾች ነበሩ፤ ክፈፎቹ ግን ባለ አራት ማእዘን እንጂ ክብ አልነበሩም።
32አራቱ መንኰራኵሮች በዕቃ ማስቀመጫው ጠፍጣፋ ናስ ሥር ሲሆኑ፣ የመንኰራኵሮቹ ወስከምቶች ደግሞ ከዕቃ ማስቀመጫዎቹ ጋር የተያያዙ ነበሩ፤ የእያንዳንዱም መንኰራኵር ስፋት አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 33መንኰራኵሮቹ የሠረገላ መንኰራኵር መሰል ሲሆኑ፣ ወስከምቶቹ የመንኰራኵሮቹ ክፈፎችና ዐቃፊዎቻቸው እንዲሁም ወስከምቶቹ የሚገቡባቸው ቧምቧዎች በሙሉ ከቀለጠ ብረት የተሠሩ ነበሩ።

34እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ወጣ ያለ እጀታ ነበረው። 35በዕቃ ማስቀመጫው ጫፍ ላይ ግማሽ ክንድ
0.2 ሜትር ያህል ነው።
የሆነ ዙሪያ ክብ ነበረበት፤ ድጋፎቹና ጠፍጣፋ ናሶቹ ከዕቃ ማስቀመጫው ዐናት ጋር የተያያዙ ነበሩ።
36እርሱም በድጋፎቹና በጠፍጣፋ ናሶቹ ላይ ባለው ቦታ ሁሉ፣ ዙሪያውን የአበባ ጕንጕን እያደረገ ኪሩቤልን፣ አንበሶችንና የዘንባባ ዛፎችን ቀረጸ። 37ዐሥሩም የዕቃ ተሸካሚዎች የተሠሩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ሁሉም ከአንድ ቅርጽ ቀልጠው የወጡ ስለሆነ፣ በመጠንና በቅርጽ ፍጹም ተመሳሳይ ነበሩ።

38ከዚያም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ የሚሆን፣ እያንዳንዱ ስምንት መቶ ሰማንያ ሊትር የሚይዝ ዐሥር የናስ መታጠቢያ ገንዳ ሠራ፤ ስፋቱም አራት ክንድ ነበር። 39ከዕቃ ማስቀመጫዎቹም አምስቱን ከመቅደሱ በስተ ደቡብ፣ አምስቱን በስተ ሰሜን በኩል አኖረ፤ ገንዳውንም ከቤተ መቅደሱ በደቡብ ምሥራቅ ጫፍ ላይ በስተ ደቡብ አኖረው። 40እንዲሁም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችንና ድስቶችን ሠራ።

ኪራምም በዚህ ሁኔታ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ እንደሚከተለው ፈጸመ፤

41ሁለቱን ምሰሶዎች፣
በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ በክብ ቅርጽ የተሠሩ ሁለት ጕልላቶችን፤
በምሰሶዎቹ ላይ ያሉትን በክብ ቅርጽ የተሠሩትን ሁለት ጕልላት ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤
42በምሰሶዎቹ ዐናት ላይ ያሉትንና ክብ ቅርጽ የያዙትን፣ በሁለት ረድፍ የተቀረጹትን መረቦች፣ የሚያስጌጡትን አራት መቶ ሮማኖች፤
43ዐሥሩን የዕቃ ማስቀመጫዎች፣ ከዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎቻቸው ጋር፤
44ገንዳውንና በሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች፤
45ድስቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን።

ኪራም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለና ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር።
46ንጉሡም እነዚህን በማቅለጥ በሸክላ ቅርጽ ውስጥ ፈስሰው እንዲወጡ ያደረገው በሱኮትና በጻርታን መካከል ባለው በዮርዳኖስ ሸለቆ ነበር። 47ሰሎሞን ከብዛታቸው የተነሣ እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች እንዲመዘኑ አላደረገም፣ ስለዚህም የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበረ አልታወቀም።

48እንዲሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት እንዲውሉ ከዚህ የሚከተሉትን ዕቃዎች ሁሉ ሠራ፤

የወርቅ መሠዊያን፣
ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥበትን የወርቅ ጠረጴዛ፤
49በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በቀኝ፣ አምስቱ በግራ የሚቀመጡ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞችን፣ ከወርቅ የተሠሩ አበቦችን፣ የመብራት ቀንዲሎችንና መቈስቈሻዎችን፤
50የንጹሕ ወርቅ ሳሕኖችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችንና ጭልፋዎችን፣
የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።

51ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር የለየውን ብሩንና ወርቁን እንዲሁም ዕቃውን አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አኖረ።

Copyright information for AmhNASV