2 Kings 14
የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ
14፥1-7 ተጓ ምብ – 2ዜና 25፥1-4፡11-12 14፥8-22 ተጓ ምብ – 2ዜና 25፥17–26፥2 1የእስራኤል ንጉሥ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ ነገሠ። 2በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ። እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። 3እርሱም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ነገር ግን አባቱ ዳዊት እንደ አደረገው ዐይነት አልነበረም፤ በማናቸውም ረገድ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ። 4በየኰረብታው ላይ ያሉት ማምለኪያዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በየኰረብታው ላይ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጤሱን እንደ ቀጠለ ነበር።5አሜስያስ መንግሥቱን አጽንቶ ከያዘ በኋላ፣ ንጉሡን አባቱን የገደሉትን ሹማምት ገደላቸው፤ 6ይሁን እንጂ በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እግዚአብሔር፣ “እያንዳንዱ በራሱ ኀጢአት ይገደል እንጂ አባቶች በልጆቻቸው፣ ልጆችም በአባቶቻቸው ኀጢአት አይገደሉ” ▼ ሲል ያዘዘ በመሆኑ፣ የነፍሰ ገዳዩን ልጆች አልገደላቸውም።
7የጨው ሸለቆ በተባለው ቦታ ዐሥር ሺሕ ኤዶማውያንን ድል ያደረገ፣ ሴላን በጦርነት የያዘና እስከ ዛሬም ድረስ ዮቅትኤል ተብላ የምትጠራበትን ስም ያወጣላት አሜስያስ ነው።
8ከዚያም አሜስያስ የኢዩ የልጅ ልጅ፣ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ዮአስ፣ “ናና ፊት ለፊት ይዋጣልን” ሲል መልእክተኞች ላከበት።
9የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ግን ለይሁዳ ንጉሥ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል ላከበት፤ “አንድ የሊባኖስ ኵርንችት፣ ለአንድ የሊባኖስ ዝግባ፣ ‘ሴት ልጅህን ለልጄ በሚስትነት ስጠው’ አለው፤ ከዚያም አንድ የሊባኖስ ዱር አውሬ መጥቶ ኵርንችቱን በእግሩ ረገጠው። 10በርግጥ ኤዶምን ድል አድርገሃል፤ ልብህ አለመጠን አይኵራራ። ድል በማድረግህ አትንጠራራ፤ ዐርፈህ ተቀመጥ! ጠብ በመጫር የራስህን፣ የይሁዳንስ ውድቀት ለምን ትሻለህ?”
11አሜስያስ ግን አልሰማም፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ወጣ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ምድር በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ጦርነት ገጠሙ።
12ይሁዳ በእስራኤል ድል ሆነ፤ እያንዳንዱም ወደ ድንኳኑ ሸሸ። 13የእስራኤል ንጉሥ ዮአስም የአካዝያስን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአስን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ አሜስያስን ቤትሳሚስ ላይ ማረከው። ከዚያም ዮአስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ ከኤፍሬም ቅጥር በር አንሥቶ የማእዘን ቅጥር በር እስከ ተባለው ድረስ ርዝመቱ አራት መቶ ክንድ ▼
▼ዕብራይስጡ 180 ሜትር ይላል።
የሆነውን ቅጥር አፈረሰ። 14በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች ያለውን ወርቅና ብር በሙሉ፣ በዚያም የተገኘውን ዕቃ ሁሉ በመውሰድ ምርኮኞችንም ይዞ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። 15በዮአስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር፣ ያደረገውና የፈጸመው ሁሉ በይሁዳ ንጉሥ በአሜስያስ ላይ ያደረገው ጦርነት ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 16ዮአስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ከእስራኤል ነገሥታት ጋር ተቀበረ፤ ልጁ ኢዮርብዓምም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። 17የኢዮአስ ልጅ የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም የእስራኤል ንጉሥ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ ከሞተ በኋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ። 18በአሜስያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 19አሜስያስ በኢየሩሳሌም ሤራ ስለ ጠነሰሱበት ሸሽቶ ወደ ላኪሶ ሄደ፤ እነርሱ ግን የሚከታተሉት ሰዎች ወደዚያው ልከው አስገደሉት፤ 20ሬሳውም በፈረስ ተጭኖ መጥቶ በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር በኢየሩሳሌም ተቀበረ።
21ከዚያም የይሁዳ ሕዝብ በሙሉ ዕድሜው ዐሥራ ስድስት ዓመት የሆነውን ዓዛርያስን ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ፈንታ አነገሡት። 22አሜስያስ ከአባቶቹ ጋር ካንቀላፋ በኋላ ኤላትን እንደ ገና ሠርቶ ወደ ይሁዳ የመለሳት ይኸው ዓዛርያስ ▼
▼ኢዩስያስ
ነበር። የእስራኤል ንጉሥ ዳግማዊ ኢዮርብዓም
23የኢዮስያስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፣ የእስራኤል ንጉሥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በሰማርያ ነገሠ፤ አርባ አንድ ዓመትም ገዛ። 24በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልተመለሰም። 25የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በጋትሔፌር ነቢይ፣ በአማቴ ልጅ በባሪያው በዮናስ አማካይነት እንደ ተናገረው፣ ከሐማት መተላለፊያ ▼▼ሊቦ
አንሥቶ እስከ ሙት ባሕር ▼▼የዓረባ ባሕር
ድረስ የነበረውን የእስራኤልን ድንበር ያስመለሰ ኢዮርብዓም ነው። 26ባሪያም ይሁን ነጻ ዜጋ፣ በእስራኤል የሚኖር ሁሉ እንዴት እጅግ ይሠቃይ እንደ ነበር እግዚአብሔር አየ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም። 27ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የእስራኤልን ስም ከምድረ ገጽ እንደሚያጠፋ ስላልተናገረ፣ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም አማካይነት ታደጋቸው።
28በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር፣ የፈጸመው ሁሉና ያደረጋቸው ጦርነቶች እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩትን ደማስቆንና ሐማትን እንዴት ለእስራኤል እንዳስመለሰ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 29ኢዮርብዓም ከአባቶቹ ከእስራኤል ነገሥታት ጋር አንቀላፋ፤ ልጁ ዘካርያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
Copyright information for
AmhNASV