Exodus 37
የኪዳኑ ታቦት
37፥1-9 ተጓ ምብ – ዘፀ 25፥10-20 1ባስልኤል ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል ▼▼ከፍታው 1.1 ሜትር ወርዱና ርዝመቱ 0.7 ሜትር ያህል ማለት ነው።
፣ ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት ሠራ። 2በውስጥና በውጭ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት። 3አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርቶ ሁለት ቀለበቶችን በአንድ በኩል፣ ሁለት ቀለበቶችንም በሌላ በኩል አድርጎ ከአራቱ እግሮቹ ጋር አያያዛቸው። 4ከዚያም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 5መሎጊያዎቹንም መሸከሚያ እንዲሆኑ በታቦቱ ጐንና ጐን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። 6ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ▼
▼ርዝመቱ 1.1 ሜትር ወርዱ 1.1 ሜትር ያህል ማለት ነው።
፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ከንጹሕ ወርቅ የስርየት መክደኛ ሠራ። 7ከዚያም ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሁለት ኪሩቤልን ከመክደኛው ጫፎች ላይ ሠራ። 8አንዱን ኪሩብ በአንዱ ጫፍ ላይ፣ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ጫፍ ላይ ሠራ፤ ከሁለቱ ጫፎች ላይ ከክዳኑ ጋር አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው፤ 9ኪሩቤልም የስርየት ክዳኑን በመሸፈን ክንፋቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ነበር፤ ኪሩቤል ወደ ስርየት መክደኛው እየተመለከቱ እርስ በርሳቸው ገጽ ለገጽ ነበሩ። የኅብስት ማስቀመጫው ጠረጴዛ
37፥10-16 ተጓ ምብ – ዘፀ 25፥23-29 10ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ከፍታውም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሠሩ ▼▼በዚህና በቍጥር 11-29 ባሉት ክፍሎች፣ ሥሩ
። 11ከዚያም በንጹሕ ወርቅ በመለበጥ በዙሪያው የወርቅ ክፈፍ አበጁለት። 12በዙሪያውም ስፋቱ አንድ ስንዝር ▼▼ወደ 8 ሳንቲ ሜትር ያህል ማለት ነው።
የሆነ ጠርዝ በማበጀት በጠርዙ ላይ የወርቅ ክፈፍ አደረጉበት። 13ለጠረጴዛው አራት የወርቅ ቀለበቶች አበጅተው አራቱ እግሮች ካሉበት ከአራቱ ማእዘኖች ጋር አያያዟቸው። 14ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች እንዲይዙ ቀለበቶቹ ከጠርዙ አጠገብ ሆኑ። 15ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች ከግራር ዕንጨት የተሠሩና በወርቅ የተለበጡ ነበሩ። 16የጠረጴዛውን ዕቃዎች ይኸውም ዝርግ ሳሕኖችን፣ ድስቶችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን እንዲሁም የመጠጥ መሥዋዕቱ ማፍሰሻ የሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠሯቸው። መቅረዙ
37፥17-24 ተጓ ምብ – ዘፀ 25፥31-39 17መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩት፤ መቆሚያውንና ዘንጉን ቀጥቅጠው አበጁት፤ የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጽዋዎች፣ እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር። 18ሦስቱ በአንድ በኩል ሦስቱ በሌላ በኩል በመሆን ስድስት ቅርንጫፎች ከመቅረዙ ጐኖች ተሠርተው ነበር። 19ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች በአንዱ ቅርንጫፍ ላይ፣ ሦስቱ ደግሞ በሚቀጥለው ቅርንጫፍ ላይ ነበሩ፤ ከመቅረዙ ለወጡት ለስድስቱም ቅርንጫፎች ሁሉ እንዲሁ ነበር። 20እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ያሉባቸው የለውዝ አበባ የሚመስሉ አራት ጽዋዎች በመቅረዙ ላይ ነበሩ። 21አንደኛው እንቡጥ ከመቅረዙ ወጣ ብለው በሚገኙት በመጀመሪያው ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር፣ ሁለተኛውም እምቡጥ በሁለተኛው ጥንድ ሥር እንዲሁም ሦስተኛው እንቡጥ በሦስተኛው ጥንድ ሥር ነበር፤ በስድስቱም ቅርንጫፎች እንዲሁ ነበር። 22እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ ተሠርተው ከመቅረዙ ጋር አንድ ወጥ ነበሩ።23የመቅረዙን ሰባት መብራቶች፣ እንዲሁም መኰስተሪያዎችንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ። 24መቅረዙንና ዕቃዎቹን ሁሉ ከአንድ መክሊት ▼
▼ወደ 34 ኪሎ ግራም ያህል ማለት ነው።
ንጹሕ ወርቅ ሠሩ። የዕጣን መሠዊያው
37፥25-28 ተጓ ምብ – ዘፀ 30፥1-5 25የዕጣን መሠዊያውን ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ ርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ከፍታው ሁለት ክንድ ▼▼ርዝመቱ ወርዱ 0.5 ሜትር ከፍታው 0.9 ሜትር ያህል ማለት ነው።
ነበር፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር። 26ላዩን፣ ጐኖቹን ሁሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጧቸው፤ በዙሪያው የወርቅ ክፈፍ አበጁ። 27ለሸክም የሚሆኑትን መሎጊያዎች ለመያዝ ትይዩ የሆኑ ከክፈፉ ሥር ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠሩ። 28መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ በወርቅም ለበጧቸው። 29እንዲሁም የተቀደሰውን ቅብዐ ዘይትና የሽቶ ቀማሚ ሥራ የሆነውን፣ ንጹሕና መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣን ሠሩ።
Copyright information for
AmhNASV