Joel 3
የተፈረደባቸው ሕዝቦች
1“በዚያ ዘመን፣ በዚያ ጊዜ፣የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮ ስመልስ፣
2አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤
ወደ ኢዮሣፍጥም ▼
▼ኢዮሣፍጥ፣ የስሙ ትርጕም እግዚአብሔር ይፈርዳል ማለት ነው፤ 12 ላይም እንዲሁ፤
ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ስለ ርስቴ፣ ስለ ሕዝቤ፣ ስለ እስራኤል፣
በዚያ ልፈርድባቸው እገባለሁ፤
ምድሬን ከፋፍለዋል፤
ሕዝቤንም በሕዝቦች መካከል በታትነዋልና።
3በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤
ወንዶች ልጆችን በዝሙት ዐዳሪዎች ለወጡ፤
ወይን ጠጅ ለመጠጣትም፣
ሴቶች ልጆችን ሸጡ።
4“ጢሮስና ሲዶና እንዲሁም እናንተ የፍልስጥኤም ግዛቶች ሁሉ ሆይ፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ምን አላችሁ? ስላደረግሁት ነገር ብድር ልትመልሱልኝ ነውን? የምትመልሱልኝ ከሆነ፣ በፍጥነትና በችኰላ እናንተ ያደረጋችሁትን በራሳችሁ ላይ መልሼ አደርግባችኋለሁ። 5ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፤ የተመረጠውንም ንብረቴን ተሸክማችሁ ወደ ቤተ መቅደሳችሁ አስገብታችኋልና። 6ከገዛ ምድራቸው ልታርቋቸው፣ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለግሪኮች ሸጣችኋቸው።
7“እነሆ፤ እነርሱን ከሸጣችሁባቸው ቦታዎች አነሣሣቸዋለሁ፤ እናንተም ያደረጋችሁትን በገዛ ራሳችሁ ላይ እመልስባችኋለሁ። 8ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻችሁን ለይሁዳ ሰዎች ሸጣለሁ፤ እነርሱም መልሰው በሩቅ ላሉት ለሳባ ሰዎች ይሸጧቸዋል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና።
9በሕዝቦች መካከል ይህን ዐውጁ፤
ለጦርነት ተዘጋጁ፤
ተዋጊዎችን አነሣሡ፤
ጦረኞችም ሁሉ ቀርበው ያጥቁ።
10ማረሻችሁ ሰይፍ፣
ማጭዳችሁም ጦር እንዲሆን ቀጥቅጡት፤
ደካማውም ሰው፣
“እኔ ብርቱ ነኝ” ይበል።
11እናንት በዙሪያ ያላችሁ ሕዝቦች ሁላችሁ፤
ፈጥናችሁ ኑ፤ በዚያም ተሰብሰቡ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ተዋጊዎችህን ወደዚያ አውርድ!
12“ሕዝቦች ይነሡ፤
ወደ ኢዮሣፍጥም ሸለቆ ፈጥነው ይውረዱ፤
ዙሪያውን ባሉት ሕዝቦች ሁሉ ላይ ልፈርድ፣
በዚያ እቀመጣለሁና።
13ማጭዱን ስደዱ፤
መከሩ ደርሷልና፤
ኑ ወይኑን ርገጡ፤
የወይን መጭመቂያው ሞልቶ፣
ከጕድጓዶቹም ተርፎ ፈስሷልና፤
ክፋታቸው እንደዚህ ታላቅ ነው።”
14ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ፣
ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ ተሰብስቧል፤
ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ፣
የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና።
15ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤
ከዋክብትም ከእንግዲህ አያበሩም።
16 እግዚአብሔር ከጽዮን ጮኾ ይናገራል፤
ከኢየሩሳሌም ያንጐደጕዳል፤
ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤
እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፣
ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።
በረከት ለእግዚአብሔር ሕዝብ
17“ከዚያም እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር፣በቅዱሱ ተራራዬ በጽዮን እንደምኖር ታውቃላችሁ፤
ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፤
ከእንግዲህም ወዲያ ባዕዳን አይወርሯትም።
18“በዚያ ጊዜ ተራሮች፣ አዲስ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤
ኰረብቶችም ወተት ያፈስሳሉ፤
በይሁዳ ያሉ ሸለቆዎች ▼
▼ወይም የሸጢም ሸለቆ
ሁሉ ውሃ ያጐርፋሉ፤ከእግዚአብሔር ቤት ምንጭ ይፈልቃል፤
የሰጢምን ሸለቆ ያጠጣል።
19ግብፅ ባድማ፣
ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች፤
በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስ፣
በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና።
20ይሁዳ ለዘላለም፣
ኢየሩሳሌምም ለትውልድ ሁሉ መኖሪያ ትሆናለች፤
21ደማቸውን እበቀላለሁ፤
በደለኛውንም ንጹሕ አላደርግም።”
እግዚአብሔር በጽዮን ይኖራል!
Copyright information for
AmhNASV