Leviticus 23:37-40

37“ ‘የሚቃጠል መሥዋዕትንና የእህል ቍርባንን፣ መሥዋዕትንና የመጠጥ ቍርባንን በተመደበላቸው ቀን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት ለማቅረብ፣ የተቀደሱ ጉባኤዎችን የምታውጁባቸው የእግዚአብሔር (ያህዌ) በዓላት እነዚህ ናቸው። 38እነዚህ መሥዋዕቶች ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ሰንበት ከምታቀርቡት፣ ከስጦታችሁ፣
ወይም እነዚህ በዓላት ከእግዚአብሔር ሰንበታት በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው፤ ስጦታዎቹም
ከስእለታችሁና ከበጎ ፈቃድ ስጦታችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ስጦታዎች ናቸው።

39“ ‘የምድራችሁን ፍሬ ከሰበሰባችሁ በኋላ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ አምስተኛው ቀን ጀምራችሁ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በዓል አክብሩ፤ የመጀመሪያው ቀን የዕረፍት ዕለት ነው፤ ስምንተኛውም ቀን እንደዚሁ የዕረፍት ዕለት ይሆናል። 40በመጀመሪያው ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ፣ የለመለመ ዛፍ ቅርንጫፍ የአኻያ ዛፍ ቅርንጫፍ ይዛችሁ ሰባት ቀን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ደስ ይበላችሁ።
Copyright information for AmhNASV