Proverbs 31
ንጉሥ ልሙኤል የተናገራቸው ምሳሌዎች
1ንጉሥ ልሙኤልን እናቱ ያስተማረችው ቃል ይህ ነው፤2“ልጄ ሆይ፤ የማሕፀኔ ልጅ ሆይ፤
የስእለቴ ልጅ ሆይ፤ ▼
▼ወይም የጸሎቴ መልስ ሆይ
3ጕልበትህን በሴት አትጨርስ፤
ብርታትህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ አታውል።
4“ልሙኤል ሆይ፤ ነገሥታት ይህን ማድረግ የለባቸውም፤
ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፣
ገዦችም የሚያሰክር መጠጥ ሊያስጐመጃቸው አይገባም፤
5አለዚያ ጠጥተው የሕጉን ድንጋጌ ይረሳሉ፤
የተጨቈኑትን ሁሉ መብት ይገፍፋሉ።
6ለሚጠፉት የሚያሰክር መጠጥ፣
በሥቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤
7ጠጥተው ድኽነታቸውን ይርሱ፤
ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ።
8“ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣
ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።
9ተናገር፤ በቅንነትም ፍረድ፤
የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”
መዝጊያ ክፍል፤ ጠባየ መልካም ሚስት
10ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ▼▼ከ10-31 ያለው እያንዳንዱ ቍጥር የሚጀምረው በዕብራይስጡ ሆህያት ቅደም ተከተል መሠረት ነው።
ከቀይ ዕንእጅግ ትበልጣለች።
11ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤
የሚጐድልበትም ነገር የለም።
12በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣
መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።
13የበግ ጠጕርና የተልባ እግር መርጣ፣
ሥራ በሚወዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች።
14እንደ ንግድ መርከብ፣
ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች።
15ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤
ለቤተ ሰቧ ምግብ፣
ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች።
16ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤
በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች።
17ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤
ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው።
18ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤
በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም።
19በእጇ እንዝርት ትይዛለች፤
በጣቶቿም ዘንጉን ታሾራለች።
20ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣
እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች።
21በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤
ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና።
22ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤
ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች።
23ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከል
በአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው።
24የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤
ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች።
25ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤
መጭውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች።
26በጥበብ ትናገራለች፤
በአንደበቷም ቀና ምክር አለ።
27የቤተ ሰቦቿን ጕዳይ በትጋት ትከታተላለች፤
የስንፍና እንጀራ አትበላም።
28ልጆቿ ተነሥተው ቡርክት ይሏታል፤
ባሏም እንዲሁ፣ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤
29“ብዙ ሴቶች መልካም አድርገዋል፤
አንቺ ግን ሁሉንም ትበልጫለሽ።”
30ቍንጅና አታላይ ነው፤ ውበትም ይረግፋል፤
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት።
31የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤
ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።
Copyright information for
AmhNASV