Proverbs 9
ጠቢብነትና ተላላነት
1ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አቆመች፤
2ፍሪዳዋን ዐረደች፤ የወይን ጠጇን ጠመቀች፤
ማእዷንም አዘጋጀች።
3ሴት አገልጋዮቿንም ላከች፤
ከከተማዪቱም ከፍተኛ ቦታ ተጣራች።
4እርሷም ማመዛዘን ለጐደላቸው፣
“ማስተዋል የሌላችሁ ሁሉ ወደዚህ ኑ” አለች።
5“ኑ፤ ምግቤን ተመገቡ፤
የጠመቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።
6የሞኝነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤
በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።”
7ፌዘኛን የሚገሥጽ ሁሉ ስድብን በራሱ ላይ ያመጣል፤
ክፉውን ሰው የሚዘልፍ ሁሉ ውርደት ያገኘዋል።
8ፌዘኛን አትዝለፈው፤ ይጠላሃል፤
ጠቢብን ገሥጸው፤ ይወድድሃል።
9ጠቢብን አስተምረው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤
ጻድቁን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀቱን ይጨምራል።
10“የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤
ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው።
11ዘመንህ በእኔ ምክንያት ይረዝማልና፤
ዕድሜም በሕይወትህ ላይ ይጨመርልሃል።
12ጠቢብ ብትሆን ጥበበኛነትህ ለራስህ ነው፤
ፌዘኛ ብትሆን የምትጐዳው ያው አንተው ነህ።”
13ጥበብ የለሽ ሴት ለፍላፊ ናት፤
እርሷም ስድና ዕውቀት የለሽ ናት።
14በቤቷ ደጃፍ ላይ ትጐለታለች፤
በከተማዪቱ ከፍተኛ ቦታ በመቀመጫ ላይ ትቀመጣለች።
15በዚያ የሚያልፉትን፣
መንገዳቸውን ይዘው የሚሄዱትን ትጣራለች።
16እርሷም ማመዛዘን ለጐደላቸው፣
“ማስተዋል የሌላችሁ ሁሉ ወደዚህ ኑ” ትላለች።
17“የስርቆት ውሃ ይጣፍጣል፤
ተሸሽገው የበሉት ምግብ ይጥማል።”
18እነርሱ ግን ሙታን በዚያ እንዳሉ፣
ተጋባዦቿም በሲኦል ▼
▼ወይም መቃብር
ጥልቀት ውስጥ እንደ ሆኑ አያውቁም።
Copyright information for
AmhNASV