‏ Proverbs 21

1የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤
እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሰኘው ይመራዋል።
2ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤
እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።

3ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።

4ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣
የክፉዎችም መብራት ኀጢአት ናቸው።

5የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤
ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።

6በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣
በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።
አንዳንድ የዕብራይስጥ ጽሑፎች፣ የሰብዓ ሊቃናትና የቩልጌት ትርጕሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አያሌ የዕብራይስጥ ጽሑፎች ግን ሞትን ለሚሹ በንኖ እንደሚጠፋ ተን ነው ይላሉ።


7ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤
ቅን ነገር ማድረግ አይወድዱምና።

8የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤
የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው።

9ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣
በጣራ ላይ ጥግ ይዞ መኖር ይሻላል።

10ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤
ባልንጀራውም ከእርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም።

11ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤
ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል።

12ጻድቁ
ወይም ጻድቁ ሰው
የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤
ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል።

13ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣
እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።

14በስውር የተደረገ ስጦታ ቍጣን ያበርዳል፤
በጕያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቍጣን ጸጥ ያደርጋል።

15ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሰኘዋል፤
ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።

16የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣
በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

17ቅንጦትን የሚወድድ ይደኸያል፤
የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድድም ባለጠጋ አይሆንም።

18ክፉ ሰው ለጻድቅ፣
ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል።

19ከጨቅጫቃና ከቍጡ ሚስት ጋር ከመኖር፣
በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።

20በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤
ተላላ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።

21ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤
ሕይወትን ብልጽግናንና
ወይም ጽድቅን
ክብርን ያገኛል።

22ጠቢብ የኀያላንን ከተማ ቅጥር ጥሶ ይገባል፤
መታመኛ ምሽጋቸውንም ያፈርሳል።

23አንደበቱንና ምላሱን የሚቈጣጠር፣
ራሱን ከመቅሠፍት ይጠብቃል።

24ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው “ፌዘኛ” ይባላል፤
በጠባዩም እብሪተኛ ነው።

25ታካችን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤
እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።

26ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤
ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።

27የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤
በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!

28ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤
ወይም የታዛዥ ሰው ቃል ግን ጸንቶ ይኖራል

እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል።

29ክፉ ሰው በዐጕል ድፍረት ይቀርባል፤
ቅን ሰው ግን አደራረጉን ያስተውላል።

30 እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣
አንዳችም ጥበብ፣ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።

31ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤
ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
Copyright information for AmhNASV