Psalms 112
የጻድቅ ሰው ባሕርይ
1ሃሌ ሉያ። ▼▼እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ነው።
እግዚአብሔርን የሚፈራ፣
በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ የተባረከ ነው።
2ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤
የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤
ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።
4ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣
ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
5ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣
ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል፤
6ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤
ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል።
7ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤
ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።
8ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤
በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
9በልግስና ለድኾች ሰጠ፤
ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤
ቀንዱም ▼
▼በዚህ ስፍራ ክብርን ያመለክታል።
በክብር ከፍ ከፍ ይላል።10ክፉ ሰው ይህን በማየት ይበሳጫል፤
ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፤
የክፉዎችም ምኞት ትጠፋለች።
Copyright information for
AmhNASV