‏ Psalms 114

ለፋሲካ የቀረበ ውዳሴ

1እስራኤል ከግብፅ ወጥቶ ሲሄድ፣
የያዕቆብም ቤት ቋንቋው ልዩ ከሆነ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ፣
2ይሁዳ የእግዚአብሔር መቅደስ፣
እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።

3ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤
ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
4ተራሮች እንደ አውራ በግ፣
ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ።

5አንቺ ባሕር፤ የሸሸሽው አንቺም ዮርዳኖስ ያፈገፈግሽው ለምንድን ነው?
6እናንተ ተራሮች እንደ አውራ በግ፣
ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ለምን ዘለላችሁ?

7ምድር ሆይ፤ በጌታ ፊት፣
በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፤
8እርሱ ዐለቱን ወደ ኵሬ፣
ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ።
Copyright information for AmhNASV