‏ Psalms 120

የሰላም ፀሮች

መዝሙረ መዓርግ።

1በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤
እርሱም መለሰልኝ።
2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣
ከአታላይ ምላስም አድነኝ።

3ሐሰተኛ አንደበት ሆይ፤ ምን ይከፈልህ?
ከዚህስ የባሰ ምን ይደረግብህ?
4በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣
በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል።

5በሜሼክ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ!
6ሰላምን በሚጠሉ መካከል፣
ነፍሴ እጅግ ብዙ ጊዜ ኖረች።
7እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፤
እነርሱ ግን በተናገርሁ ጊዜ ጠብ ይሻሉ።
Copyright information for AmhNASV