‏ Psalms 126

የስደት ተመላሾች መዝሙር

መዝሙረ መዓርግ።

1 እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ
ወይም እግዚአብሔር ሀብቷን ይመልሳል።
በመለሰ ጊዜ፣
ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።
ወይም የሰዎቿ ጤንነት ይታደሳል።

2በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣
አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤
በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣
እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
3 እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤
እኛም ደስ አለን።

4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በኔጌቭ እንዳሉ ጅረቶች፣
ምርኳችንን መልስ።
ወይም ሀብታችንን መልስ

5በእንባ የሚዘሩ፣
በእልልታ ያጭዳሉ።
6ዘር ቋጥረው፣
እያለቀሱ የተሰማሩ፣
ነዷቸውን ተሸክመው፣
እልል እያሉ ይመለሳሉ።
Copyright information for AmhNASV