Psalms 129
በጽዮን ጠላቶች ላይ የቀረበ ጸሎት
መዝሙረ መዓርግ።
1እስራኤል እንዲህ ይበል፦“ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤
2በርግጥ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤
ዳሩ ግን ድል አላደረጉኝም።
3ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤
ትልማቸውንም አስረዘሙት።”
4 እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው፤
የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለው።
5ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣
ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
6ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣
በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤
7ደግሞም ለዐጫጅ እጁን፣
ለነዶ ሰብሳቢ ዕቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።
8መንገድ ዐላፊዎችም፣
“የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤
በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ።
Copyright information for
AmhNASV