‏ Psalms 132

የክብረ በዓል መዝሙር

132፥8-10 ተጓ ምብ – 2ዜና 6፥41-42

መዝሙረ መዓርግ።

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ዳዊትን፣
የታገሠውንም መከራ ሁሉ ዐስብ፤
2እርሱ ለእግዚአብሔር ማለ፤
ለያዕቆብም ኀያል አምላክ እንዲህ ሲል ተሳለ፤
3“ወደ ቤቴ አልገባም፤
ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤
4ለዐይኖቼ እንቅልፍን፣
ለሽፋሽፍቶቼም ሸለብታ አልሰጥም፤
5 ለእግዚአብሔር ስፍራን፣
ለያዕቆብም ኀያል አምላክ ማደሪያን እስካገኝ ድረስ።”

6እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤
በቂርያትይዓሪም
አንዳንዶቹ ያዓር ይላሉ።
አገኘነው።
7“ወደ ማደሪያው እንግባ፤
እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ፤
አንተና የኀይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ሂዱ።
9ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤
ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”

10ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል፣
የቀባኸውን ሰው አትተወው።

11 እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤
በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤
“ከገዛ ራስህ ፍሬ፣
በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።
12ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣
የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣
ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣
ለዘላለም ይቀመጣሉ።”

13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፣
ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወድዷልና እንዲህ አለ፤
14“ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤
ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ።
15እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ፤
ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ።
16ለካህናቷ ድነትን አለብሳለሁ፤
ቅዱሳኗም በደስታ ይዘምራሉ።

17“በዚህም ለዳዊት ቀንድ
እዚህ ላይ ቀንድ የጥንካሬ ትእምርት ሲሆን፣ ንጉሥን ያመለክታል።
አበቅላለሁ፤
ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ።
18ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባቸዋለሁ፤
እርሱ ግን በራሱ ላይ የደፋው ዘውድ ያበራል።”
Copyright information for AmhNASV