Psalms 133
የወንድማማች ፍቅር
የዳዊት መዝሙረ መዓርግ።
1ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣
እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!
2በራስ ላይ ፈስሶ፣
እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣
እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣
እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው።
3ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ፣
እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤
በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን፣
ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዟልና።