‏ Psalms 141

የክፉዎችን ድሎት ላለመመኘት የቀረበ ጸሎት

የዳዊት መዝሙር።

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤
ወደ አንተ ስጣራም ድምፄን ስማ።
2ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ትቈጠርልኝ፤
እጄን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።

3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤
የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
4ከዐመፀኞች ጋር፣
በክፉ ሥራ እንዳልተባበር፣
ልቤን ወደ ክፉ አታዘንብል፤
ከድግሳቸውም አልቋደስ።

5ጻድቅ
ወይም ጻድቁ
ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤
ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤
ራሴም ይህን እንቢ አይልም።
ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው፤
6ሹማምታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፤
ቃሌ የምታረካ ናትና ይሰሟታል።
7ደግሞም፣ “ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣
እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል
አንዳንድ ትርጕሞች መቃብር ይላሉ።
አፋፍ ላይ ተበታተነ” ይላሉ።

8ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ፤
መጠጊያዬም አንተ ነህ፤ እንግዲህ ነፍሴን አትተዋት።
9ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣
ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ።
10እኔ ብቻ በደኅና ሳመልጥ፣
ክፉዎቹ በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ።
Copyright information for AmhNASV