Psalms 144
የጦርነት መዝሙር
የዳዊት መዝሙር።
1እጆቼን ለጦርነት፣ ጣቶቼን ለውጊያ የሚያሠለጥን፣እግዚአብሔር ዐለቴ ይባረክ።
2እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤
ምሽጌና ታዳጊዬ፣
የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤
ሕዝቤን የሚያስገዛልኝም ▼
▼አንዳንዶች ሕዝቦችን የሚያሰገዛልኝ ይላሉ።
እርሱ ነው።3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው?
4ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤
ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያትህን ሰንጥቀህ ውረድ፤
ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስስ።
6የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤
ፍላጻህን ሰድደህ ግራ አጋባቸው።
7እጅህን ከላይ ዘርጋ፤
ከኀይለኛ ውሃ፣
ከባዕዳንም እጅ
ታደገኝ፤ አድነኝም።
8አንደበታቸው ሐሰትን ይናገራል፤
ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት።
9አምላክ ሆይ፤ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ፤
ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።
10ነገሥታትን ድል የሚያጐናጽፍ፣
ባሪያውን ዳዊትን ከሚጐዳ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።
11አንደበታቸው ሐሰትን ከሚናገር፣
ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው፣
ከባዕዳን እጅ
ታደገኝ፤ አድነኝም።
12ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣
የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣
ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ
እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ።
13ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣
የተሞሉ ይሁኑ፤
በጎቻችን እስከ ሺሕ ይውለዱ፤
በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺሕ ይባዙ።
14ከብቶቻችን ይክበዱ፤ ▼
▼ወይም መሪዎቻችን ይጠነክራሉ።
አይጨንግፉ፤ አይጥፉም።
እኛም በምርኮ አንወሰድ፤
በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይሰማ።
15ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው፤
እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው።
Copyright information for
AmhNASV