‏ Psalms 150

የምስጋና መዝሙር

1ሃሌ ሉያ።
አንዳንዶች ከ6 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።


እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤
በታላቅ ጠፈሩ አወድሱት።
2ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤
እጅግ ታላቅ ነውና ወድሱት።
3በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤
በበገናና በመሰንቆ ወድሱት።
4በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤
በባለ አውታር መሣሪያና በእንቢልታ አወድሱት።
5ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤
ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል ወድሱት።

6እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።

ሃሌ ሉያ።
Copyright information for AmhNASV