Psalms 16
እግዚአብሔር ርስቴ
የዳዊት ቅኔ።
1አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣በከለላህ ሰውረኝ።
2 እግዚአብሔርን፣ “አንተ ጌታዬ ነህ፤
ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም”
አልሁት።
3በምድር ያሉ ቅዱሳን፣
ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው። ▼
▼ወይም በምድሪቱ ላሉ አረማውያን፣ ካህናትና ደስ ለተሰኙባቸው መኳንንት ሁሉ ይህን እላለሁ
4ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣
ሐዘናቸው ይበዛል፤
እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስስም፤
ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፤
5 እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤
ዕጣዬም በእጅህ ናት።
6መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤
በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።
7የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤
በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።
8 እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤
እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
9ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤
ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
10በሲኦል ▼
▼ወይም በመቃብር
ውስጥ አትተወኝምና፤ቅዱስህም ▼
▼ወይም በአንተ የታመነውን
መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።11የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ ▼
▼ወይም ታሳውቀኛለህ
በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣
በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።
Copyright information for
AmhNASV