Psalms 29
ለማዕበሉ ጌታ የቀረበ ውዳሴ
የዳዊት መዝሙር።
1እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።
2ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤
በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
3 የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤
እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።
4 የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤
የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው።
5 የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል።
6ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣
ስርዮንንም ▼
▼አርሞንዔም የተባለው ተራራ ነው።
እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።7 የእግዚአብሔር ድምፅ
የእሳት ነበልባል ይረጫል።
8 የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤
የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9 የእግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤ ▼
▼ወይም እግዚአብሔር አጋዘን እንድትወልድ ያደርጋል
ጫካዎችንም ይመነጥራል፤
ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።
10 እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል፤ ▼
▼ወይም ይቀመጣል
እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
11 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።
Copyright information for
AmhNASV