‏ Psalms 80

ለእስራኤል ተሐድሶ የቀረበ ጸሎት

ለመዘምራን አለቃ፤ “የኪዳን ጽጌረዳ” በሚለው ቅኝት የሚዜም፤ የአሳፍ መዝሙር።

1ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣
የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤
በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፤
በብርሃንህ ተገለጥ።
2በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይ።
ኀይልህን አንቀሳቅስ፤
መጥተህም አድነን።

3አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤
እንድንም ዘንድ፣
ፊትህን አብራልን።

4የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤
በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነድደው፣
እስከ መቼ ድረስ ነው?
5የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤
ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።
6ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤
ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን።

7የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤
እንድንም ዘንድ፣
ፊትህን አብራልን።

8ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ፤
አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት።
9መሬቱን መነጠርህላት፤
እርሷም ሥር ሰድዳ አገሩን ሞላች።
10ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤
ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።
11ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣
ሜድትራኒያን ሳይሆን አይቀርም።

ቍጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ
የኤፍራጥስ ወንዝ ለማለት ነው።
ዘረጋች።

12ታዲያ ዐላፊ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲለቅም፣
ለምን ቅጥሯን አፈረስህ?
13ዕርያ ከዱር ወጥቶ ያበለሻሻታል፤
በሜዳ የሚንጋጋ እንስሳ ሁሉ ይበላታል።
14የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤
ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤
ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤
15ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ቡቃያ፣
ለራስህ ያጸደቅሃት ተክል
ወንድ ልጅ የሚሉ ትርጕሞች አሉ።
ናት።

16እርሷም በእሳት ተቃጥላለች፤
የግንባርህ ተግሣጽ ያጠፋቸዋል።
17ለራስህ ባበረታኸው የሰው ልጅ ላይ፣
በቀኝ እጅህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን።
18ከእንግዲህ አንተን ትተን ወደ ኋላ አንመለስም፤
ሕያዋን አድርገን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን።

19የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልሰን፤
እንድንም ዘንድ፣
ፊትህን አብራልን።
Copyright information for AmhNASV