Psalms 81
ለዳስ በዓል የሚዜም ቅኔ
ለመዘምራን አለቃ፤ በዋሽንት የሚዜም፣ የአሳፍ መዝሙር።
1ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ፤ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ።
2ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤
በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ።
3በሙሉ ጨረቃ፣ በክብረ በዓላችን ዕለት፣
በወሩ መግቢያ፣ ጨረቃ ስትወለድ መለከት ንፉ፤
4ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ሥርዐት፣
የያዕቆብም አምላክ ድንጋጌ ነውና።
5ሙሉ ለሙሉ ግብፅን ለቅቆ በወጣ ጊዜ፣
ይህን ለዮሴፍ ደነገገለት፤
በማላውቀውም ▼
▼አንዳንዶች የማናውቀውን ድምፅ ሰማን ይላሉ።
ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤6“ትከሻውን ከሸክም ገላገልሁት፤
እጁንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ።
7በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግሁህ፤
በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ፤
በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ። ሴላ
8“ሕዝቤ ሆይ፤ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ፤
እስራኤል ሆይ፤ ምነው ብታደምጠኝ!
9በአንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አይኑር፤
ለሌላም አምላክ አትስገድ።
10ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤
አፍህን በሰፊው ክፈተው፤ እኔም እሞላዋለሁ።
11“ሕዝቤ ግን አላደመጠኝም፤
እስራኤልም እጅ አልሰጥ አለኝ።
12ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣
አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው።
13“ምነው ሕዝቤ ቢያደምጠኝ ኖሮ፣
እስራኤል በመንገዴ በሄደ ኖሮ፣
14ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባንበረከክኋቸው ነበር፤
እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ ባነሣሁ ነበር።
15 እግዚአብሔርን የሚጠሉ በፊቱ ይርዳሉ፤
ቅጣታቸውም እስከ ዘላለም የሚዘልቅ ነው።
16እናንተን ግን ምርጡን ስንዴ አበላችኋለሁ፤
ከዐለቱም ማር አጠግባችኋለሁ።”
Copyright information for
AmhNASV