‏ Psalms 82

ሙሱናን ዳኞች

የአሳፍ መዝሙር።

1እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ መካከል ተሰየመ፤
በአማልክትም ላይ ይፈርዳል፤ እንዲህም ይላል፤
2“ፍትሕን የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው?
ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው? ሴላ
3ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ ዐደጎች ፍረዱላቸው፤
የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ።
4ወገን የሌለውንና ችግረኛውን ታደጉ፤
ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።

5“ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤
በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤
የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።

6“እኔም፤ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤
ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ’ አልሁ።
7ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤
እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።”

8አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ በምድር ላይ ፍረድ፣
ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና።
Copyright information for AmhNASV