Psalms 93
የእግዚአብሔር ግርማ
1 እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤
ብርታትንም ታጠቀ፤
ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤
ማንም አይነቀንቃትም።
2ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤
አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤
ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤
ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ።
4ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ፣
ከባሕርም ሞገድ ይልቅ፣
ከፍ ብሎ ያለው እግዚአብሔር ኀያል ነው።
5ሥርዐትህ የጸና ነው፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣
ቤትህ በቅድስና ይዋባል።
Copyright information for
AmhNASV