Psalms 30
ከክፉ አደጋ የዳነ ሰው ምስጋና
ለቤተ መቅደሱ ምረቃ የተዘመረ፤ የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከታች አንሥተኸኛልና፣ጠላቶቼም በላዬ እንዳይደሰቱ አድርገሃልና፣
ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
2 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ ጮኽሁ፤
አንተም ፈወስኸኝ።
3 እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን ከሲኦል ▼
▼ወይም ከመቃብር
አወጣሃት፤ወደ ጕድጓድ ከመውረድም መልሰህ ሕያው አደረግኸኝ።
4እናንተ ቅዱሳኑ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
ቅዱስ ስሙንም አወድሱ።
5ቍጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤
ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤
ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣
በማለዳ ደስታ ይመጣል።
6እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣
“ከቶ አልናወጥም” አልሁ።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣
ተራሮቼ ▼
▼ወይም ኰረብታማ የሆነች አገሬ
ጸኑ፣ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣
ውስጤ ታወከ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤
ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤
9“በእኔ ወደ ጕድጓድ መውረድ፣
በመሞቴ ምን ጥቅም ይገኛል? ▼
▼ወይም ዝም ብል…ይገኛል?
ዐፈር ያመሰግንሃልን?
ታማኝነትህንስ ይናገራልን?
10 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማ፤ ማረኝም፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ረዳት ሁነኝ።”
11ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ፤
ማቄን አውልቀህ ፍሥሓን አለበስኸኝ፤
12እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።
Copyright information for
AmhNASV